Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ የመስክ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ የመስክ ጉብኝት አደረጉ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የግምባር ቀደም አርሶ አደሮችን የቡና ማሳ የጎበኙ ሲሆን አርሶ አደሮቹ የተሻሻሉ ዝርያዎችን በመጠቀምና ያረጁ ቡናዎችን በመጎንደል ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል።

የክልሉ መንግስት በዚህ አመት ለቡና ልማት 147 ሚሊየን ብር መመደቡን የገለፁት አቶ ሽመልስ፥ የገበያ ትስስር ለማጠናከር ለባለሀብቶችና የህብረት ስራ ማህበራት ብድር የሚውል 15 ቢሊየን ብር መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በመሆኑም የጅማ ዞን አርሶ አደሮች የቡናን ጥራት በመጠበቅና ለአቮካዶና ሌሎች ቅመማ ቅመሞች እንዲሁም ለንብ ማነብ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።

 

በሙክታር ጠሃ

You might also like
Comments
Loading...