Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ከመቐሌ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር ከመቐሌ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ።

በዚሁ ወቅት የመቐሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ሀገሪቱ ለዩኒቨርሲቲው እያደረገች ላለችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በውይይቱ ላይ በኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት ሂደት ዙርያ አመራሮቹ ያላቸውን ሙያዊ እይታ ላይ ምክክር ያደረጉ ሲሆን፥ ፕሮፌሰር ክንደያ እና የዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ምሁር መረሳ ፀሃየ በጉዳዩ ላይ ለአምባሳደሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በውይይቱ ላይ የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳም በጉዳዩ ዙርያ የትግራይ መንግስት እና ህዝብ ሃሳብን ገልፀዋል።

You might also like
Comments
Loading...