Fana: At a Speed of Life!

ናሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶች ብቻ የተሳተፉበት የህዋ ጉዞ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 10፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ናሳ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች ብቻ የተመራ የህዋ ጉዞ በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን አስታውቋል።

የጠፈር ጉዞውን ያከናወኑት ባለሙያዎችም ክሪስቲና ኮች እና ጀሲካ ሚዬር የተባሉ ሴት ተመራማሪዎች መሆናቸው  ተገልጿል።

ክሪስቲና ኮች ወዳ ጠፈር ስትጓዝ አምስተኛ ጊዜዋ ሲሆን ፥ጀሲካ ሚዬር ደግሞ የመጀመሪያዋ ነው ተብሏል።

ሴት የጠፈር ተመራማሪዎቹ ወደ ህዋ ያቀኑትም በዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ያገጠመን የባትሪ ችግር ለመፍታት መሆኑ ተመላክቷል።

ይህም በናሳ ታሪክ ወደ ህዋ ከተደረጉ ጉዞዎች ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች ብቻ የተካሄደ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

ሴት የጠፈር ተመራማሪዎቹ የህዋ ጉዟቸውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸው ተከትሎም  የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ  እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋቸዋል ።

ፕሬዚዳንቱ ለጠፈር ተመራማሪዎች  በስልክ ባስተላለፉት መልዕክት ፥ የሚገርምና አስደናቂ ታሪክ ያስመዘገባችሁ ጎበዝ ሴቶች  ናቸሁ  በማለት አድንቀዋቸዋል ።

 

ምንጭ ፦አናዶሉ

 

You might also like
Comments
Loading...