Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕ ጀግና ለተባለው  ውሻ ሜዳሊያ እንደሰጡ የሚያሳይ ሀሰተኛ ፎቶ መልቀቃቸው እያነጋገረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶናልድ ትራምፕ አል ባግዳዲን ለመግደል በተካሄደው ዘመቻ ተሳትፎ ለነበረው ውሻ ሜዳሊያ ሲሰጡ የሚሳይ የተቀነባረ ፎቶ በመልቀቃቸው ተቃውሞ እየቀረበባቸው ነው

ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ የለቀቁት ፎቶ በአይ ኤስ መሪ አል ባግዳዲ ግድያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበረው ጀግና ውሻ  በአንገቱ ላይ ሜዳሊያ ሲያጠልቁለት ያሳያል፡፡

ነገር ግን ይህ ፎቶ በተግባር ያልተደረገ እና አሶሴትድ ፕሬስ በ2017 ጄሜስ ማክክሎከን የክብር ሜዳሊያ ሲበረከትላቸው የሚያሳየውን ፎቶ በማቀነባበር የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡

አል ባግዳዲ በተገደለበት ዘመቻ ላይ ተሳትፎ የነበረው ይህ ውሻ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት እንዳልገባ እና ጉዳት አጋጥሞት የነበረ ቢሆንም  ወደ ሌላኛው ሃላፊነት መሰማራቱ ነው የተነገረው፡፡

ይህ የፕሬዚዳንት ተግባርም በአሁን ወቅት ከፍተኛ ችግር የሆነው የሀሰተኛ ዜናዎች መገለጫ ነው በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡

ጄሜስ ማክክሎከን ም ፎቶዋቸውን ተቀነባብሮ ጥቅም ላይ በማወሉ ምን አይነት ምላሽ እንዳልሰጡና  በተግባሩ እንደተስማሙ ይመስላል የሚል ግምት እየተሰጠ ነው፡፡

ምንጭ፡- ሃፊንግተንፓስት

You might also like
Comments
Loading...