Fana: At a Speed of Life!

በጋሞ ዞን የሞተር ጀልባ ሰጥሞ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን የሞተር ጀልባ ሰጥሞ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

አደጋው በትናንትናው እለት ከቀኑ 9 ሰዓት ከሎካ አባያ ወደ አርባምንጭ 6 ሰዉ ጭኖ ሲመጣ የነበረ ሞተር ጀልባ ላይ መድረሱን የዞኑ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል።

በአደጋውም በሞተር ጀልባው ተሳፍረው ሲጓዙ ከነበሩት ውስጥ የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰው መትረፉን የጋሞ ዞን ሠላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ ገልፀዋል።

ችግሩ የተከሰተው በወቅቱ በተነሳው ማእበል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ከአደጋው የተረፈው ግለሰብ ጀሪካን ተጠቅሞ በመዋኘቱ ህይወቱ መትረፉን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅትም በአደጋው ሀይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን የማፈላለግ ስራ እየተሰራ ሲሆን፥ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የጋሞ ዞን፣ የአርባምንጭ ከተማ እና ዙሪያ ወረዳ ፓሊስ አባላት በፍለጋ ላይ መሆናቸውም ተነግሯል።

የጋሞ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተሰማውን ሐዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።

You might also like
Comments
Loading...