Fana: At a Speed of Life!

በሞዛምቢክ ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞዛምቢክ ጠቅላላ ምርጫ እያደረገች ነው።

በምርጫው የተመዘገቡ 13 ሚሊየን የሚደርሱ የሃገሬው ዜጎችም በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ እየሰጡ ነው።

ሞዛምቢክ ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ ሃገሪቱን የሚመራው ፍሬሊሞ እና ከነጻነት ማግስት በትጥቅ ትግል የቆየው ሬናሞ ዋነኛ ተፎካካሪዎች ናቸው።

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ፊሊፔ ንዩሲ ለሰላም እንደሚሰሩ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።

ሬናሞ ከገዥው ፓርቲ ጋር ለበርካታ አመታት በትጥቅ ትግል ቆይቷል።

የአሁኑ ምርጫም ፍሬሊሞ ፓርቲ የዜጎችን ይሁንታ እያጣ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ለፓርቲው መልካም አጋጣሚ ነው እየተባለ ነው።

በጋዝ ምርቷ የበለጸገችው ደቡብ አፍሪካዊቷ ሞዛምቢክ በፈረንጆቹ 1975 ከፖርቹጋል ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ ለበርካታ አመታት በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ቆይታለች።

ለ16 አመታት በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት ወደ 1 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

የእርስ በርስ ጦርነቱ በፈረንጆቹ 1992 በተኩስ አቁም ስምምነት ቢፈታም ከፍተኛ የጋዝ ክምችት ያለባቸውን አካባቢዎች ለመቆጣጠር በሚደረግ ሂደት የሚፈጠር ግጭት ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን ማድረጉ ይነገራል።

በአሁኑ የምርጫ ሂደትም አንድ የምርጫ ታዛቢ የተገደሉ ሲሆን የሬናሞ ታጣቂዎችም ጥቃት መፈጸማቸው ተነግሯል።

 

 

ምንጭ፦ ሬውተርስ

 

You might also like
Comments
Loading...