Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ ከጣሊያን ሴኔት ፕሬዚዳንት ማሪያ ኤልዛቤታ ጋር ተወያዩ

አዲስ አባበ፣ ጥቅምት 4፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጣሊያን ሴኔት ፕሬዚዳንት ማሪያ ኤልዛቤታ አልበርቲ ጋር በጣሊያን ሮም ተወያይተዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የሚመራ የመንግስት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ሮም በሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት ጣሊያን ሮም ገብቷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእስካሁን የሮም ቆዩታቸውም ከጣሊያን ሴኔት ፕሬዚዳንት ማሪያ ኤልዛቤታ አልበርቲ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት የልማት ትብብር እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በቀጣይ የሀገራቱን ውጤታማ የኢኮኖሚ እና የኢቨንስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንት ማሪያ ኤልዛቤታ በበኩላቸው በምስራቅ አፍሪካ የተረጋጋ ሰላም እና ቀጠናዊ ትብብር እንዲሳለጥ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት የምትጫወተውን ሚና አድንቀዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸውን አስመልክተው ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like
Comments
Loading...