Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በመጀመሪያው ሩብ አመት ከ57 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት ከ57 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ አመት 56 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 57ነጥብ3 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ነው ያስታወቀው፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አበቤ ሰራተኛውና አመራሩ ስራውን በብቃት መስራቱ እና ግብር ከፋዩ ግብሩን በተማኝነትና በወቅቱ መክፈሉ ለዕቅዱ መመሳካት ጉልህ ሚና እንደነበረው ተናግረዋል፡፡

የቀጣይ የጥቅምት ወር የገቢ እቅድ ካለፉት ወራቶች ከፍተኛ ስለሆነ ሰራተኛውና አመራሩ ጠንክሮ በመስራት ፤ግብር ከፋዩም ግብሩን በወቅቱ በመከፈል ለዕቅዱ ስኬ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

አፈፃፀም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ12ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለውም ነው ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው፡፡

በሀምሌ ወር 18 ቢሊዮን፣ በነሀሴ ወር 20ነጥብ2 ቢሊዮን እና በመስከረም 19ነጥብ1 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡም ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህም መካከል 54 በመቶ ያህሉ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን÷ ቀሪው 46 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከጉምሩክ ገቢ የተሰበሰበ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ በዚሁ ሩብ ዓመት የማስተማር እና ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራዎችን በማከናዎን በተጨማሪ ሀሰተኛ ደረሰኝ በመጠቀም ግብይት የፈፀሙ 16 ድርጅቶች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል፡፡

በግብይት ወቅት ደረሰኝ የማይቆርጡ ድርጅቶች ላይ የኢንተለጀንስ ስራ በመስራት 50 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል 2ነጥብ6 ሚሊየን ብር አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲቀጡ አድርጓል፡፡

You might also like
Comments
Loading...