Fana: At a Speed of Life!

ለ40 ዓመት በዘለቀው የቀይ ቀለም ልዩ ፍቅር ቀይ ሃውልት ከወዲሁ ያዘጋጁት እናት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዞሪካ ረበርኒክ የተባሉት የ67 ዓመት አዛውንት በቦሲኒያ ብረዜ በተባለችው ትንሽ ከተማ ነዋሪ ናቸው።

ለቀይ ቀለም ካላቸው ልዩ ፍቅር የተነሳ ላለፉት አራት አስርት አመታት አልባሳትን ጨምሮ ቀይ ቀለም ከሌላቸው መጠቀሚያ ቁሳቁሶች ውጭ እንደማይጠቀሙ ተነግሯል።

በቀይ ብርሃን ውስጥ እንደሚኖሩ የተነገረላቸው አዛውንቷ መንፈሳቸው ከቀይ ቀለም ጋር እንዴት ሊቆራኝ እንደቻለ በውል እንደማያውቁት ይናገራሉ።

ይሁን እንጂ ገና በ18 ዓመታቸው ነው የሚለብሷቸውን አልባሳት፣ የቤት መጠቀሚያ ቁሳቁሶች፣ መዋቢያ ቁሳቁሶቻቸውን፣ የክፍላቸውን ቀለም ምርጫ ቀይ ማድረግ መጀመራቸውን የሚናገሩት፡፡

በሰርግ ቀናቸው ሳይቀር ቀይ ቬሎ መልበሳቸውን በማስታወስ፤ ላለፉት 40 ዓመታት ፀጉራቸውን የሚያቀልሙት በቀይ ቀለም፣ የሚጠጡት በቀይ ብርጭቆ፣ የሚመገቡት በቀይ ሳህን መሆኑ ተገልጿል።

አሁን ላይ ከመምህርነት ስራ በጡረታ ተገልለው የሚገኙት አዛውንቷ ቀብር ስርዓት ላይ በሚታደሙበት ወቅትም ቀይ ቀል ቀለም ያላቸው አልባሳት ለብሰው ነው ተብሏል፡፡

በአዛውንቷ ክፍል  ውስጥ አንድ ነጭ ማሞቂያ ብቻ ለምልክት የምትገኝ ሲሆን፥ ይህች ማሞቂያ በባለቤታቸው ግፊት ወደ ቤታቸው መግባቷን ነው የሚናገሩት።

አዛውንቷ ዘላቂ ማራፊያቸውን ማለትም የቀብር ስፍራቸውን ከዚሁ ቀይ ቀለም ጋር በማያያዝ ለእርሳቸው እና ለባለቤታቸው ከቀይ ግራናይት የተሰራ የቀብር ሃውልት ከወዲሁ ማዘጋጀታቸውም ተነግሯል።

ምንጭ፦ odditycentral.com

You might also like
Comments
Loading...