Fana: At a Speed of Life!

ለአትሌቲክስ ቡድኑ ሽልማት እና እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዶሃ ለተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ልዑካን የሽልማትና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ።

ቡድኑ በውድድሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማምጣት አጠናቋል።

ምሽቱንም በኤሊያና ሆቴል የእውቅናና ሽልማት ስነ ስርአት ተካሂዷል።

በውድድሩ ለተሳተፈው ቡድን በሽልማት መልክ ከ2 ነጥብ 25 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት ተሰጥቶታል።

የወርቅ ሜዳሊያ ያመጡ 40 ሺህ ብር፣ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ ያመጡት ደግሞ እያንዳንዳቸው በቅደም ተከተል 30 ሺህ እና 20 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

You might also like
Comments
Loading...