Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የኢንፌክሽን መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መመሪያ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የኢንፌክሽን መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መመሪያ ማዘጋጀቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሀገር አቀፍ የኢንፌክሽን እና መቆጣጠሪያ መመሪያ ሀገራዊ የትውውቅ አውደ ጥናት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የስብሰባ አዳራሽ ተካሂዷል።

በአውድ ጥናቱ ላይ ከሁሉም ክልል ጤና ቢሮ፣ ከሆስፒታሎች፣ ከአለም ጤና ድርጅት እና አጋር ድርጅቶች ጥሪ የተደረገላቸው  ተካፋዮች ተገኝተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ይህ የኢንፌክሽን መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መመሪያ የታካሚዎችን ደህንነትን ለመጠበቅ የሚረዳ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ዶክተር ያእቆብ ሰማን፥ የጤናው ዘርፍ ስራዎች ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ የታካሚዎች ደህንነት መጠበቅ እና የተዋህሲያንን መድሃኒት መለማመድ መቻልን ለመከላከል  ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው መሆኑን በአጽንኦት አስረድተዋል፡፡

የጤና ተቋማት ንፁህ፣ ምቹና ሳቢ እንዲሆኑ ካስፈለገ ሣይንሳዊ የሆነ የአሰራር ስርዓቶችን መከተል እንዲሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡

መመሪያው የአለም ጤና ድርጅት አለም አቀፋዊ መስፈርቶች እና የአሰራር መመሪያዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እንደተዘጋጀ ከጤና ሚኒስቴ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like
Comments
Loading...