Fana: At a Speed of Life!

2019 በታሪክ ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች የሞቱበት አመት ሆኖ ተመዘገበ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፈረንጆቹ 2019 በታሪክ ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች የሞቱበት አመት ሆኖ መመዝገቡን አለም አቀፉ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን አስታወቀ፡፡

በዚህ አመት 49 ጋዜጠኞች በዓለም ዙሪያ መሞታቸውን ያስታወቀው ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን ይህም ባለፉት 16 ዓመታት ውስጥ ከተመዘገቡት የጋዜጠኞች ሞት ዝቅተኛው ሊሆን ችሏል ብሏል፡፡

በታሪክ ዝቅተኛ ቁጥር የተባለለት የ2019 የጋዜጠኞች ሞት አብዛኛው የተመዘገበው በየመን ፣ ሶሪያ እና አፍጋኒስታን ውስጥ ዘገባ ላይ በነበሩ ጋዜጠኞች ላይ የተከሰተ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ፓሪስ ላይ መሰረቱን ያደረገው ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድንም የጋዜጠኝነት ሥራ አደገኛ ሙያ ነው ሲል አስታውቋል፡፡

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ በአማካይ ወደ 80 የሚጠጉ ጋዜጠኞች ሕይወታቸውን ያጡ እንደነበር  ተገልጿል፡፡

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን ሃላፊ ክሪስቶፍ ዴሎሬ ÷ በአንጻራዊ ሰላም  ናቸው በሚባሉ ሀገራት የሚገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን ÷ በማሳያነትም በሜክሲኮ ብቻ 10 ጋዜጠኞች መገደላቸውን በመግለፅ  አስጠንቅቀዋል ፡፡

በግጭት ዞኖች ውስጥ የሟቾች ቁጥር የሚጠበቅ ቢሆንም ፤ በዴሞክራሲያዊት አገሮች ውስጥ በሠሩት ሥራ የሚገደሉ  ጋዜጠኞች ቁጥራቸው እየጨመረ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

14 ሪፖርተሮች የተገደሉበት ላቲን አሜሪካ  ለጋዜጠኞች እንደ መካከለኛው ምስራቅ የሞት ቀጠና እየሆነ ነው ተብሏል፡፡

ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ጋዜጠኞች እስር ቤቶች  ከገቡ በኋላ እንደሚሞቱ   ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን አስታወቋል ፡፡

በፈረንጆቹ  2019 ወደ 389 ያህል ሰዎች  የታሰሩ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት 12 በመቶው አድጓል ፡፡

ከታሳሪዎቹ ግማሽ የሚሆኑት ጋዜጠኞች በቻይና ፣ ግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ ሲሆን እንደሚታወሰው ሳዑዲ አረቢያ   ባለፈው ዓመት በኢስታንቡል በሚገኘው ኤምባሲዋ አምደኛ ጀማል ካሾጊጊ ገድላዋለች በሚል ክስ ይቀርብባታል፡፡

ቻይና ብቻዋን በአለም ከታሰሩት ጋዜጠኞች መካከል  አንድ ሶስተኛውን ይዛለች፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ 57 ጋዜጠኞች በዓለም ዙሪያ በተለይም በሶሪያ ፣ በየመን ፣ ኢራቅ እና ዩክሬን ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው ይገኛሉ ፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.