Fana: At a Speed of Life!

በግብጽ አመጽ እና ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግብጽ ሁለተኛ ቀኑን የያዘ አመጽ እና ግጭት መቀስቀሱ ተነግሯል፡፡

በወደብ ከተማዋ ሲዊዝ 200 ያህል ተቃዋሚዎች ጎዳና ላይ ወጥተው ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡

በተቃዋሚዎች እና የጸጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት መከሰቱን እና ፖሊስ አስለቃሽ ጪስ መጠቀሙ ነው የተነገረው፡፡

በርካታ ተቃዋሚዎች በጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

የአልስሲሲ አስተዳደር ግን በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል ነው የተባለው፡፡

በአሳለፍነው አርብም በተመሳሳይ መልኩ ግብፃአውያን በካይሮ ታህሪር አደባባይ ወጥተው በአልሲስ አስተዳዳር የሙስና ተግባር ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ በበኩላቸው ውንጀላውን እንዳልተቀበሉት ነው ዘገባው የሚየስረዳው፡፡

ምንጭ፡- ቢ ቢ ሲ

You might also like
Comments
Loading...