Fana: At a Speed of Life!

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ።

ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋርም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ በጉብኝቱ ተካተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ለሁለት አስርት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ከታደሰ በኋላ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።

በአሁኑ ጉብኝታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.