Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ አስተዳዳር በዓሉን ከህሙማንና ድጋፍ ከሚያሰፈልጋቸው ወገኖች ጋር አከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎንደር ከተማ አስተዳዳር በየዘመን መለወጫ በዓልን ከህሙማን እና ድጋፍ ከሚያሰፈልጋቸው ወገኖች ጋር አከበረ።

የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን አዳነ እና የከተማው አመራሮች የጎንደር ዩኒቨርስቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ሲሳይ ይፍሩ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታልና መና የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን እና የነገ ተስፋ የህፃናት ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በህሙማን የመርጃ ማዕከሉ የምሳ ግብዣ ተደርጓል።

የበግና ሌሎች ስጦታም ተበርክቷል።

የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን አዳነ፥ አዲሱ ዓመት ያለንን የምናካፍልበት፣ ለሀገራችን ሰላም እና አንድነትና ብልፅግና የምንሰራበት እንዲሆን ተመኝተዋል።

በነብዩ ዮሃንስ

You might also like
Comments
Loading...