Fana: At a Speed of Life!

ክርስቲያን ላጋርድ አፍሪካ የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አህጉር እንድትሆን ጥሪ አቀረቡ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) የቀድሞዋ ዋና ዳይሬክተር ክርስቲያን ላጋርድ አፍሪካ የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አህጉር እንድትሆን ጥሪ አቀረቡ፡፡

አህጉሪቷ የመልማት አቅሟን ለመጠቀም የጥይት ድምጽ የማይሰማባት ማድረጉ ቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በሃላፊነት በቆዩበት የስምንት ዓመታት ተሞክሯቸው ዙሪያም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም በአፍሪካ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በተለያዩ ግጭቶች መፈናቀላቸውን አውሰተዋል፡፡

መፈናቃሉ በተቀባይ ሀገራት ዘንድ ጫና እንዳለውም አስረድተዋል፡፡

ለዚህም ባለፉት ጊዚያት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ደቡብ ሱዳን ብቻ 3 ሚሊየን ያህል ዜጎች መፈናቀላቸውን አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጅ በአንዳድ የአፍሪካ ሀገራት አንፃራዊ መሻሻሎች መታየታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

የኢኮኖሚ እድገት እየተመዘገበ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በተለይም ለኢኮኖሚ እድገቱ ጠቃሚ በሆኑ ፖሊሲዎች ዙሪያ ግንዛቤ መፈጠሩን ነው የሚናገሩት፡፡

ክርስቲያን ላጋርድ ለአውረፖ ማዕከላዊ ባንክ ፕሬዚዳንት መታጨታቸውን ተከትሎ ባሳላፍነው ሳምንት ከዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተርነታቸው መነሳታቸውን ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን አፍሪካ

You might also like
Comments
Loading...