Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክ የታክሲ ስምሪት መመሪያ በዘርፉ ተዋንያን ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሮኒክ የታክሲ ስምሪት ላይ ያወጣው መመሪያ በዘርፉ ተዋንያን ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል።

መመሪያው በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን የመረጃ ቋት የትራንስፖርት ቢሮ ክትትል እንዲደርግ የሚያድርግና በአገልግሎቱ የሚሰማሩ ተሽከርካሪዎች ኮድ አንድ ብቻ እንዲሆኑ የሚያስገድድ ነው።

በቴክኖሎጂ አገልግሎቱን ለመስጠት ግለሰብም ይሁን ተቋም ወደ አገልግሎቱ ለመሰማራት መስፈርቶቹን ማሟለት እንደሚጠበቅባቸው የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከአምስት ዓመት በፊት ወደ አገልግሎት የገባው እና ከ6 ሺህ በላይ የተሽከርካሪ ባለቤቶችን በስሩ ያቀፈው የራይድ ሥራ አስኪያጅ ሳምራዊት ፍቅሩ መመሪያው ላይ ቅሬታ ያነሳሉ።

ቅሬታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያቀረቡት የራይድ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊት ፍቅሩ፥ መመሪያው እኛ ሳያወያይ የወጣና የግለሰቦችን በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት የሚገታ ነው ይላሉ።

መመሪያው ሲወጣ መካተት የሚገባቸው አካለትን ያላካተተና መመሪያውን ለማውጣት ስልጣን ባለው አካል አይደልም የወጣው ሲሉም ተናግረዋል።

ስራ አስኪያጇ ሳምራዊት ፍቅሩ አክለውም፥ መመሪያው የግለሰቦችን እቅንስቃሴ መረጃ አሳልፎ ከመሰጠት የደነገገው ተገቢ አይደልም ነው የሚሉት።

በመመሪያው መሰረት ራይድ ዳታ ቤዙን ለትራንስፖርት ቢሮ ክፍት ያድረግ መባሉ የግለሰቦችን ሚስጥር አሳልፎቹ ስጡ እንደማላት ነው ሱሉ ያክላሉ።

ራይድ አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት፤ ታክሲ ስለጠራው ሰው ማንነት፣ ስለታክሲው አሽከርካሪ፣ ጉዞው ከየት ወደየት እንደተካሄደ የሚገልጸው መረጃ የሚከማችበት የመረጃ ቋት ቢሮ መጠየቁ ህጋዊነት እንደሌላው ያነሳሉ።

ተገልጋዮቻችን ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ሲንቀሰቀሱ መረጃውን ለሦስተኛ ወገን እንደማንሰጥባቸው አምነው ነው ብለዋል።

መረጃው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኝ የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዞ ማግኝት ይቻላል ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ መረጃውን አቅርበናል ነው የሚሉት።

የምንሰራውም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ከንግድ ሚኒስቴር ፍቃድ አውጥተን ያሉት ስራ አስኪያጇ፥ ዳግም ፍቃድ ልናወጣም አይገባም የትራንስፖርት ቢሮ ይህን መመሪያ የማውጣት ስልጣን የለውም ባይ ናቸው።

የራይድ የህግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ቶሎሳ ደሜ በበኩላቸው፥ አሁን የከተማ አስተዳድሩ ያወጣው መመሪያ የዜጎችን ሃብት የማፍራት መብት የሚጋፋ ነው።

የመዲናው የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊው ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ ደግሞ ከዚህ ቀደም በሰጡት መግለጫ፥ መመሪያው መንግስት የመቆጣጠር ሃላፊነቱን እንዲወጣ እንዲያስችለው የወጣ ነው ብለዋል።

በኤታስ አገልግሎት የሚሰማራ ተሸርካሪም ይሁን ድርጅት የወጣውን መመሪያ ተከትሎ መስራት እንደሚጠበቅበት በማንሳት።

እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ የራይድ የህግ አማካሪያ ጠበቃ ቶሎሳ ደሜ የከተማው አስተዳደሩ ያወጣው መመሪያ ኮድ 3 ታሳቢ ያደረገ አይደልም ይላሉ።

የኪራይ አገልግሎት በአገልግሎት ሰጪና ተገልጋይ መካክል በሚደረግ ስምምነት የሚከናውን ስራ ነው የሚሉት አቶ ቶሎሳ፥ አሁን ግን ህጋዊ ፍቃድ ኖራቸው በኮድ 3 የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ መስራት እየቻሉ አይደልም ይላሉ።

የከተማ አስተዳድሩ ትራንስፖርት ቢሮ በመመሪያው ላይ የሚነሱት ቅሬታዎችን የሚሰጠው ምላሽ ካለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በቀጣይ ተከታትሎ የሚያስተናግድ ይሆናል።

በበላይ ተስፋዬ

You might also like
Comments
Loading...