Fana: At a Speed of Life!

የትዊተር ኩባንያ ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ትዊተር ገፅ ተጠለፈ

አዲስ አበባ፣ነሃሴ 27፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የትዊተር ኩባንያ ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፋፃሚ ጃክ ዶርሴይ የትዊተር ገፅ መጠለፉ ተሰምቷል።

ጃክ ዶርሴይ የሚጠቀምበት ከ4 ሚሊየን ባላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር ገፅ ባሳለፍነው ዓርብ ዕለት በበይነ መረብ በርባሪዎች ከቁጥጥር ውጭ የነበረ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል።

ከትዊተር ገጹ የጠለፋ ድርጊት ጀርባም እራሳቸውን “የሳቂታዎች ቡድን” ብለው የሚጠሩት የበይነ መረብ ጥቃት አድረሾች መኖራቸው ተገልጿል።

የትዊተር ገጹን በመጥለፍ በቁጥጥር ስር ካደረጉ በኋላም የተለያዩ የጥላቻ ንግግሮችን ለተከታዮች ማሰራጨታቸው ነው የተገለጸው።

ከዚህ ባለፈም የተለያዩ የሀሰት መረጃዎችንና አስቂኝ ፅሁፎችን በትዊተር ገጹ ማሰራጨታቸውን ጃክ ዶርሴይ ተናግረዋል።

የትዊተር ገጹ ከተጠለፈ ከአንድ ስዓት ቆይታ በኋላ ማስመለስ መቻሉን የገለጹት ጃክ፥ የተሰራጩ የተለያዩ የሀሰት መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮችም ከመተግበሪያው እንዲወገዱ ተደርገዋል።

ክስተቱ ተከትሎም ትዊተር የራሱን ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፋፃሚ ገጽ ከጥቃት መከላከል ካልቻለ በደንበኞቹ  ገጽ ላይ ምን ያህል ዋስታና ሊኖረው ይችላል የሚል ትችት ቀርቦበታል።

ይሁን እንጂ  ችግሩ የተፈጠረው በትዊተር አሰራር ችግር ምክንያት አለመሆኑን ነው ዋና ስራ አስፋፃሚው ጃክ ዶርሴይ የተናገሩት።

እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚው ገለፃ ችግሩ የተፈጠረው የትዊተር ገጹ የተከፈተበት የስልክ ቁጥጥር ከሚቆጣጠረው የቴሌኮም ኩባንያ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል።

ምንጭ ፦ሬውተርስ

You might also like
Comments
Loading...