Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሌሴቶ ጋር ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 29፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ )ለ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሌሴቶ ጋር
በባህርዳር አለም አቀፍ ስታድየም ይጫወታሉ፡፡

ዋልያዎቹ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን 10 ሰዓት ላይ በርካታ ደጋፊዎች በተገኙበት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ከነሃሴ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ይህ ጨዋታ ለማሸነፍ የሚያስችለውን ውጤት ለማስመዘግብ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ለብሄራዊ ቡድኑ ጨዋታ 74 ሺህ ትኬቶች ለሽያጭ እንደተዘጋጁ የተገለፀ ሲሆን የስታድየሙ ሁሉም በሮች ከ 6 ሰዓት ጀምሮ ክፍት እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አብርሃም መብራሃቱ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሌሴቶ ጋር እንደደረሳቸው ካወቁ ጊዜ ጀምሮ ጥሩ ዝግጅት
ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከሌሴቶ ከሚያደርጉት ጨዋታ በተጨማሪ ቡርንዲ ከታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን ከ ኢኳተሪያል ጊኒ፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪሲፔ ከጊኒ ቢሳው ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

You might also like
Comments
Loading...