Fana: At a Speed of Life!

ኢንጅነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን አስመልክተው ከአባገዳዎችና ቄሮዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ መስከረም 24 ቀን በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን አስመልክተው ከአባገዳዎች፣ ቄሮዎችና ከፎሌ ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

አሁን ላይ በዓሉን አስመልክቶ እየተደረጉ ባሉ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የከተማ አስተዳደሩም የኢሬቻ በዓል ከምንጊዜውም በላይ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

አባገዳዎቹ በበኩላቸው በዓሉ ደማቅ እና ስኬታማ ሆኖ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢሬቻ በዓል የፊታችን መስከረም 24 ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል።

You might also like
Comments
Loading...