Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ አመት የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የሚሰራበት ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 6 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲሱ አመት የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ እንደሚሰራ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ለአዲሱ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም በአዲሱ አመት የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

የኦሮሞ ህዝብ የክረምቱ ዝናብና ጨለማ አልፎ ወደ ጸደይ ብርሃን ሲገባ፣ ጨለማውን አሳልፎ ብርሃኑን ላሳየው ዋቃ ምስጋናን ያቀርባል ብለዋል በመልዕክታቸው።

ለሰራው መልካም ሥራዎች ምስጋና በማድረስ የጎደለውን ለመሙላት ወደፊት ያልማል ብለዋል አቶ ሽመልስ ባስተላለፉት መልዕክት።

አቶ ሽመልስ አዲሱ አመት በጎ በጎውን አስበንና ሰርተን የህዝባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት የምንለውጥበትና ብሩህ ተስፋን የምንሰንቅበት ዘመን ይሁንልን በማለትም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

አያይዘውም ለህዝብ ሰርተን ለህዝብ እንኑር፣ ፍትሕን ለህዝብ ሰጥተን በፍትሐዊት እናገልግልም ነው ያሉት።

አዲሱ ዘመን እንደ ብረት በጠነከረው አንድነት የህዝቡን ሕይወት ለመቀየር ሌት ተቀን በመትጋት የህዝቡ ፍላጎት የሚሟላበት ዘመን ይሆን ዘንድም ተመኝተዋል።

ነገ የሚገባው 2012 ዓ.ም የህዝብ አንድነት ተጠናክሮ በመደመር ፍልስፍና ሃገር የሚገነባበት እና የብልጽግና፣ በአንድነት በመደመር እሳቤ፣ እጅ ለእጅ በመያያዝ ድህነትን በማስወገድ የፍስሃ ትውልድ የምናፈራበት ዘመን ይሁንልን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

 

 

 

You might also like
Comments
Loading...