Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በጉዳት ምክንያት በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻንፒዮና እንደማትሳተፍ ታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በጉዳት ምክንያት በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻንፒዮና እንደማትሳተፍ ተነግሯል።

የአትሌት ገንዘቤ ዲባባ ወኪል ኩባንያ የሆነው ፓይንዳ ስፖርት እንዳስታወቀው፥ በቀኝ እግሯ ላይ በደረሰባት ጉዳት ምክንያትነው  ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ከሚካሄደው የ2019 የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻንፒዮና ላይ የማትሳተፈው።

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ባለፈው ነሀሴ በዙሪክ ከተካሄደው የዲያመንድ ሊግ ውድድር ላይ በቀኝ እግሯ ላይ ህመም ተሰምቷት እንደነበረ መኪል ኩባንያው አስታውቋል።

ይህንን ተከትሎ በጀርመን ሙኒክ በተደረገላት ምርመራም በግራ እግሯ ላይ ጉዳት መድረሱን ነው ፓይንዳ ስፖርት ያስታወቀው።

በዚህም ምክንያት አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በአውሮፓውያኑ 2019 ለሚካሄደው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻንፒዮና እንደማትደርስ ነው ወኪል ኩባንያው ያስታወቀው።

በተመሳሳይ የኬንያው 1500 ሜትር ሻምፒዮና አትሌት ኤሊጃህ ማናምጎይ በጉዳት ምክንያት ከዶሃው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጭ መሆኑ ተሰምቷል።

You might also like
Comments
Loading...