Fana: At a Speed of Life!

በፍቅር ልባቸው ለተሰበሩ ደንበኞች ነፃ አገልግሎት የሚሰጠው ጸጉር ቤት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በፍቅር ልባቸው ለተሰበሩ ደንበኞች ነፃ አገልግሎት የሚሰጠው ጸጉር ቤት በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል።

በደቡብ ምዕራብ ቻይና ሺቿን ግዛት ቼንግዱ ከተማ የሚገኝ አንድ ጸጉር ቤት በፍቅር ልባቸው ለተሰበሩ ሰዎች ነፃ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተነግሯል።

ጸጉር ቤቱ ከሚወዷት ፍቅረኛቸው ጋር በተለያዩ ምክንያቶች ተለያይተው ልባቸው ክፉኛ የተጎዳ ደንበኞችን በነፃ ጸጉራቸውን የሚያስተካክል መሆኑ ተገልጿል።

ጸጉር ቤቱ በፍቅር ልባቸው የተሰበሩ ሰዎችን ለማፅናናት በሚያስችሉ በተለያዩ የፍቅር ጥቅሶች እና መልዕክቶች የተዋበ መሆኑም በዘገባው ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም የደንበኞችን ስሜት መያዝ የሚችሉ በጥንቃቄ የተመረጡ ለስላሳ ዘፈኖች ለደንበኞች ይጋበዛሉ።

ይህም በተለያዩ አጋጣሚዎች ፍቅረኛቸውን በድንገት ለተለዩና ከልብ የተጎዱ ሰዎችን ለማፅናናት ብሎም ወደ ቀደመ ስሜታቸው ለመመለስ በር የሚከፍት መሆኑ ተጠቁሟል።

ምንጭ ፦ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like
Comments
Loading...