Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የቺኩን ጉንያ ወረርሽኝን ለመከላከል የቤት ለቤት የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 29፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተከሰተውን የቺኩን ጉንያ ወረርሽኝ ለመከላከል ቫይረሱን የምታስተላልፈውን ትንኝ የመራባት ሂደት ለማጥፋት የቤት ለቤት የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

ርጭቱ አሁን ላይ በ4 ቀበሌዎች እየተካሄደ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ፉአድ ከድር እንደገለጹት ርጭቱ 72 ባለሞያዎችን በማሰማራት እየተካሄደ ነው::

ይህም በሽታውን የምታስተላልፈው “ኤደስ” የተሰኘችው ትንኝ የምትጥላቸውን እጮች ከመነሻው ለማጥፋት ያስችላል፡፡

በተለይም ከዝናብ ውሃ ከጣራ ላይ በአሸንዳ የሚጠራቀም ውሃ የትንኟ እጭ ሊኖሯቸው ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ነው የተገለፀው፡፡

ወረርሽኙ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ 25 ሺህ ዜጎች በወረርሽኑ መጠቃታቸው የተገለፀ ሲሆን፥ትንኟ ከዚህ ቀደም በከተማዋ የምትገኝ በመሆኗ ለስርጭቱ ከፍ ማለቱ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ 12 የጤና ባለሙያዎችን በመላክ ከቢሮው ጋር እየስራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ከባለሙያዎች ጋር በመሆን በነገው ዕለት በድሬ ዳዋ ጉብኝት በማድረግ ወረርሽኑን ለመቆጣጠር በሚሰራው ሥራ ላይ ከአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ጋር ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ የጠበቃል፡፡

በመለሰ ምትኩ

You might also like
Comments
Loading...