Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል 20 ክላሽና በርካታ ጥይቶች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ፖሊስ 20 ክላሽና አንድ ሽጉጥን ጨምሮ ከ53 ሺህ በላይ የተለያዩ መሳሪያ ጥይቶች ትናንት በኤሊደአር ወረዳ ዲቻቶ ቀበሌ መያዛቸውን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አህመድ ሁመድ ከየመን ተነስቶ በጅቡቲ በኩል ወደ መሃል ሃገር ለማስገባት በተለያዩ ቦታዎች ተደብቆ የነበረ የጦር መሳሪያ በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን ተናረዋል።

መሳሪያው የተያዘው አስመስሎ በዘይት ጀሪካንና በቃጫ በመቆጣጠር ተደብቆ ሊገባ ሲል መያዙን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተደረገው ፍተሻም 20 ክላሽና አንድ ሽጉጥን ጨምሮ 45 ሺህ 392 የክላሽ፣ 8 ሺህ 484 የኤም 14 መሳሪያ እና 45 የመትረየስ ጥይት ተይዟል ነው ያሉት።

You might also like
Comments
Loading...