Fana: At a Speed of Life!

በኒውዚላንድ በተቀሰቀሰ የኩፍኝ በሽታ ከ1ሺህ በላይ ሰዎች መታመማቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ነሃሴ 30፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኒውዚላንድ በተቀሰቀሰ የኩፍኝ በሽታ ከ1ሺህ በላይ ሰዎች መታመማቸው ተገለጸ፡፡

በኒውዚላንድ ከሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ጥር 1 ቀን 2019 እስከ ዛሬዋ ቀን ድርስ 1ሺህ 5 ሰዎች በኩፍኝ በሽታ መያዛቸው ተነግሯል፡፡

በኒውዚላንድ ኦክላንድ ከተማ ብቻ 877 የኩፍኝ ታማሚዎች ተመዝግበዋል ተብሏል፡፡

እድሚያቸው 12 ወራት እስከ 50 ዓመት ያሉ የኩፍኝ ክትባት ያልወሰዱ ዜጎች ክትባቱን እንዲወስዱ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ጥሪ ማስተላለፉም ነው የተገለጸው፡፡

ወደ ኦክላንድ ለጉብኝት የሚገቡ ጎብኝዎችም ወደዚያ ከመንቀሳቀሳቸው ሁለት ሳምት ቀደም ብለው ክትባት መከተብ እንዳለባቸውም ነው ዘገባው የሚያመላክተው፡፡

ሳል በቆዳ ላይ ሽፍታ መውጣት እና የሰውነት ትኩሳት የበሽታው ምልክቶች ሲሆኑ÷ በሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊና የህመም ስሜት የሚያስከትል ነው፡፡

የበሽታው ስርጭት ከአለፈው የአውሮፓዊያኑ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በያዝነው ዓመት የመጀመሪያ ሶሰት ወራት በአራት እጥፍ ጨምሯል ነው የተባለው፡፡

በሽታው አስተማማኝ ክትባት ያለው ቢሆንም ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ታዳጊ ሀገራት እየተከሰት እንደሚገኝም ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ፡- ቢ ቢ ሲ

You might also like
Comments
Loading...