Fana: At a Speed of Life!

በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ ማስተካከያ ሳይደረግበት ስራ ላይ እንዳይውል ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5 ፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ ማስተካከያ ሳይደረግበት ስራ ላይ እንዳይውል የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል።

65 የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀውን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው የጸደቀው ህግ የመደራጀት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብትን የሚጥስ በመሆኑ በስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል።

ከዚህ ባለፈም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ በመጀመሪያ ከቀረበውና ውይይት ከተደረገበት ረቂቅ ህግ ውጭ የተጨመሩ ሀሳቦች ስላሉበት እንደማይቀበሉት ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል።

ስለሆነም በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት እንዲሻሻል ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

You might also like
Comments
Loading...