Fana: At a Speed of Life!

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 26 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 29፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 26 ሽጉጦች ቦምባስ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ በጉምሩክ ፈታሾች እና በፌዴራል ፖሊስ አማካኝነት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በወቅቱ ከሽጉጦቹ ጋር ሁለት የሽጉጥ ሰደፍና 11 ካርታ የተያዘ ሲሆን ህገ-ወጥ መሳሪያው በአይሱዙ ተሽከርካሪ ወደ ሐረር መስመር እየተጓዘ ነበር በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው፡፡

ኮንትሮባንድ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ያስከትላል ያለው የገቢዎች ሚኒስቴር ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የህዝብ ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል ብሏል፡፡

የጥቂት ህገ-ወጦች ፍላጎት በሚያሟላው የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ ምክንያት የሀገር ሰላም እንዳይደፈርስ የሰላም ባለቤት የሆነው ህዝብ በንቃት እንዲጠብቅ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like
Comments
Loading...