Fana: At a Speed of Life!

ስናፕ ቻት የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ የሚያስችል የማስታወቂያ ቦታ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ስናፕ ቻት የፖለቲካ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶችን ለማስተላለፍ የሚያስችል የማስታወቂያ ቦታ ይፋ አድርጓል።

ስናፕ ቻት የፖለቲካ ማስታወቂያ ቦታውን ይፋ ያደረገውም በአሁኑ ወቅት የሞባይል መተግበሪያዎች ዋነኛ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ማካሄጃ መሳሪያዎች መሆናቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።

በዚህ መሰረትም ስናፕ ቻት በቀጣዩ የፈረንጆች አዲስ ዓመት ጀምሮ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች ብቻ የሚጫኑበት ቦታ በመተግበሪያው ላይ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

ይህም የፖለቲካ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ወይም ግለሰቦች ለምርጫ የሚወዳደሩበትን ርዕዮተ ዓለምና  መተዳደሪያ ደንብ ለአባሎቻቸው በቀላሉ ለማሳወቅ ያስችላል ተብሏል።

ለዚህም የፖለቲካ ፓርቲ ተወዳዳሪዎች ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልዕክት በምስል፣ በፅሁፍ አሊያም በተንቀሳቃሽ መስል በማስደገፍ ማሰራጨት ይችላል።

የማስታወቂያ ቦታው መልዕክቱን ያስተላለፈውን ፖለቲከኛ ወይም ተወዳዳሪ ማንነት የሚያሳውቁ አስፈላጊ ዝርዝር መረጃዎችን የሚያካትት መሆኑ ተመልክቷል።

ምንጭ ፦ሲ ኤን ኤን

You might also like
Comments
Loading...