Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የስራ ፈጠራ ስትራቴጅ በ 2012 ዓ.ም ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 29፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀገራዊ የስራ ፈጠራ ስትራቴጅ በ 2012 ዓ.ም ወደ ስራ እንደሚገባ የፌዴራል አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ማስፋፊያ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ከዚህ ቀደም የነበሩት አሰራሮች ስራ ፈጣሪዎችን የሚያበረታቱ ባለመሆናቸው እና ድጋፍ እንዲደረግላቸው የሚያደርጉ አሰራሮች ባለመኖራቸው በርካታ ስራ ፈጣሪዎችን ማፍራት እንዳልቻሉ ባለስልጣነ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ ገልፀዋል፡፡

ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚወጡ ተማሪዎች ሁሉም በሚባል ደረጃ የስራ ፍለጋ አማራጭ የሚያደርጉት የመንግስት የስራ ተቋማት ነው።

ከሚፈልጉት በጣም ጥቂቱ ቢሳካላቸውም በርካቶቹ ደግሞ ስራ አጥ እንዲሆኑ ይገደዳሉ።

ለዚህ ደግሞ በራሳቸው ስራ ፈጥረው እንዲሰማሩ የሚያስችሏቸው መንገዶች ስላልነበሩ መሆኑን ነው  ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

ከዚህ ቀደም የነበሩት አሰራሮች ስራ ፈጣሪዎችን የሚያበረታቱ ባለመሆናቸው እና ድጋፍ እንዲደረግላቸው የሚያደርጉ አሰራሮች ባለመኖራቸው በርካታ ስራ ፈጣሪዎችን ማፍራት አልቻልንም ብለዋል፡፡

የፌዴራል አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ማስፋፊያ ባለስልጣን ለፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሳወቀው ለስትራቴጅው ትግበራ የሚያስፈልግ ሀገራዊ እቅድ እየተዘጋጀ ነው።

ለዚህ ችግር መፍትሄ የሚሆን አሰራር በአዲሱ አመት ተግባራዊ እንደሚደረግ ባለሰልጣኑ አስታውቋል፡፡

በብሄራዊ ባንክ ተዘጋጅቶ በተጠናቀቀው በጀት አመት የፀደቀው ሀገራዊ የስራ ፈጠራ ወይም ኢንተርፕርነርሽፕ ስትራቴጅም ከዚህ ቀደም በዘርፉ የነበሩ ቸግሮቸን ለመቅረፍ የሚያስችል እንደሆነ ታምኖበታል።

ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ስትራቴጅ ስራ ፈጣሪዎች እንዴት መለየት አለባቸው፣ በምን መልኩ ነው መደገፍ ያለባቸው፣ የሚያስፈልጓቸው ድጋፎች እና ውጤታማ የሚሆኑበትን አቅጣጫዎችም የሚይዝ እና በርካታ ስራ ፈጣሪዎቸን ለማፍርት ብሎም ስራ አጥነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ቁልፍ አሰራሮቸን የያዘ  ነው።

ስትራቴጂው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶቸን በሀገር ውስጥ ማምረት የሚቻልበትን መንገድ የሚያሳይ እና ወደ ወጭ የሚላኩ ምርቶቸም ቢሆን ውጤታማ ገቢን እንዲያስገኙ ማድረግን የሚያመላከት ነው።

አቶ አስፋው እንደገለፁት በስትራቴጅው መሰረት ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት እንዲችሉ እና ወጭ ምርቶችን ደግሞ በጥራት እና በተወዳዳሪነት ቀዳሚ እንዲሆኑ ማድረግ ይችላሉ።

በአሁኑ ሰአትም ስትራቴጂው ሀገራዊ የትግበራ እቅድ እየተዘጋጀለት መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለፁት፡፡

በትግበራ እቅዱ መሰረትም ከ2012 አመተ ምህረት ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስራ አጥ የሆኑ እና ስራ መፍጠር የሚችሉ ወጣቶች ወጥ በሆነ አሰራር ይለያሉ።

የሚደረጉላቸው ድጋፎችም ወጥ እንዲሆን የማድረግ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችለው የትግበራ እቅዱ ወደ ክልሎች እደሚላክ ተጠቁሟል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

You might also like
Comments
Loading...