Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት በርንሌይ ከማንቼስተር ሲቲ በሚያደርጉት ጨዋታ ጅማሮውን ያደርጋል፡፡

በፕሪሚየርሊጉ መክፈቻ አዲስ አዳጊው በርንሌይ ከአምናው የሊጉ ሻምፒዮን ማንቼስተር ሲቲ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ይጫወታል፡፡

የቀድሞው የማንቼስተር ሲቲ ተከላካይ ቪንሰንት ኮምፓኒም በርንሌይን ይዞ በፕሪሚየር ሊጉ የአሰልጣኝነት ህይወቱን አንድ ብሎ ይጀምራል።

ፕሪሚየር ሊጉ ነገን ጨምሮ እስከ ፊታችን ሰኞ ድረስ የተለያዩ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።

ነገ አርሰናል ከኖቲንግሃም ፎረስት ሲጫወት፥ ምሽት ኒውካስትል ከአስተንቪላ የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው።

በማግስቱ እሑድ ደግሞ ቼልሲ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ሆኗል።

የምንጊዜም የክለቡን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሃሪ ኬንን ለባቫሪያኑ ክለብ ለመሸጥ የተስማማው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ደግሞ ከብሬንትፎርድ ጋር ከሜዳው ውጭ ይጫወታል።

ማንቼስተር ዩናይትድ ደግሞ ሰኞ ዎልቨርሃምፕተንን በኦልድትራፎርድ ምሽት 4 ሰአት ያስተናግዳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.