Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ከኢራን ጋር ለመነጋገር የሌሎች ፈቃድ እንደማያስፈልጋት ገለጸች

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 4 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ በአሜሪካና በኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ለምታደርገው ጥረት የሌሎች ይሁንታ እንማደማያስፈልጋት አስታወቀች፡፡

ፈረንሳይ ይህን ያለችው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፈረንሳዩ አቻቸው ላይ በዋሽንግተን እና በቴህራን ጉዳዮች ጣልቃ በመግባት ውንጀላ ማቅረባቸውን ተክትሎ ነው ተብሏል፡፡

ሀገሪቱ የቀጠናውን ውጥረት ለማረጋጋት ሁኔታዎችን በማመቻቸት ጠንካራ እንደምትሰራ የፈረንሳዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን የቨስ ሌ ዳሪን በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ፈረንሳይ ለቀጠናው ሰላም እና ደህነት ለመስራትም ፈቃድ እንደማያስፈልጋት ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳላፍነው ሃሙስ የኢራን ባለስልጣናት ከአሜሪካ ጋር የመነጋገር ፍላጎት ቢያሳዩም ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጨምሮ እኛ እንወክላለን የሚሉ አካላት ጣልቃ እየገቡብን ነው ሲሉ ውንጀላ አቅርበዋል፡፡

ለአሜሪካ ማንም ሊናገርላት አይችልም ያሉት ትራምፕ በፈለገው መንገድ ሊያስተካክለን ወይም ሊወክለን የሚችል አካል ሊኖር አይችልም ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢራን የአሜሪካ ሰው አልባ የቅኝት አውሮፕላን ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ሰኔ ወር መታ ከጣለች በኋላ በአጸፋው አሜሪካ በቴህራን እና መሪዎቿ ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል፡፡

በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካካል የነበረው ቅራኔ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት ግንቦት ወር 2018 ዋሽንግተን ከቴህራን ጋር ከተፈራራመችው የኒውክሌር ስምምነት መውጣቷን ይፋ አድርጋለች፡፡

ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ብሪታኒያ፣ ቻይና እና ሩሲያ ይህን ሃሳብ እንዳልደገፉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ከዚህ ሳምንት በፊትም የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከኢራኑ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሩሃኒ ጋር የስልክ ግንኙነት ማድረጋቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like
Comments
Loading...