Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ አፍሪካ የታንዛኒያን አውሮፕላን በቁጥጥር ስር አዋለች

አዲስ አበባ፣ነሃሴ 19፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት የታንዛኒያ ብሔራዊ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን አውሮፕላን በጆሃንስበርክ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታውቀዋል።

ኤየር ባስ 220-300 የተሰኘው የታንዛኒያ አውሮፕላን በቁጥጥር ስር የዋለውም ባሳለፈነው ዓርብ ዕለት ከጆሃንስበርግ ወደ ዳሬሳላም ለመብረር በዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።

ይሁን እንጂ  ደቡብ አፍሪካ  አውሮፕላኑን በቁጥጥር ስር ያዋለችበት ምክንያት በዘገባው አልተገለጸም።

የሀገሪቱ  ባለስልጣናትም አውሮፕላኑ በቁጥጥር ስር የዋለበትን ምክንያት ከመግለፅ ተቆጥበዋል ነው የተባለው።

በሌላ በኩል አውሮፕላኑ በቁጥጥር ስር የዋለው የታንዛኒያ መንግስት ለደቡብ አፍሪካ አርሶ አደሮች ሊከፍለው የሚገባውን 33 ሚሊየን ዶላር ባለመክፈሉ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

የታንዛኒያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደርገውን በረራ ከሁለት ወራት በፊት መጀመሩ ይታወሳል።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...