Fana: At a Speed of Life!

የ50 ዓመት ጓደኛሞቹ የ2 ሚሊየን ዶላር ሎተሪን ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 22፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ50 ዓመታት የዘለቀ ጓደኝነት ያላቸው ካናዳውያን የ2 ሚሊየን ዶላር የሎተሪ እጣን ለሁለት መጋራተቸው የብሪትሽ ኮሎምቢያ ሎተሪ አስተዳደር አስታውቋል።

ሱዛን ሁክ እና ማርታ ኤምሲካለም የተባሉ ካናዳውያን ጓደኛሞች ናቸው የሎተሪ እጣውን ለሁለት የተጋሩት።

በመጀመሪያ የሆነውን ማመን ተስኖን ነበር ያሉት ጓደኛሞቹ፥ ሁለቱም በጋራ የሎተሪ አሸናፊ መሆናቸው እንዳስደሰታቸው አስታውቀዋል።

ባገኙት ገንዘብም ኑሯቸውን ማመቻቸት እና የተለያዩ ጉዞዎችን በማድረግ ዓለምን የመጎብኘት እቀድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd

You might also like
Comments
Loading...