Fana: At a Speed of Life!

የ4 ቢሊየን የችግን መርሃ ግብር ሙሉ ለሙሉ ተሳክቷል – ብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ4 ቢሊየን የችግኝ መርሃ ግብር ሙሉ ለሙሉ መሳካቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ የችግኝ መርሃ ግብሩ አስተባባሪ ብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የችግኝ ተከላ ማሳረጊያ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡

በዚህ ወቅት የ4 ቢሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተተከሉ የችግኝ አይነቶች እና ብዛት የማጣራት ስራ እንደሚካሄድ ነው የተነገረው፡፡

በክረምቱ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ 60 በመቶ የሚሆኑት ለጥምር ግብርና የሚያገለግሉ ሲሆን 40 በመቶዎቹ ደግሞ ለደን የሚሆኑ ችግኞች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይነትም ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በተቀናጀ ሁኔታ እንደሚከናወን ነው የተገለፀው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ  አባላት ጋር በመሆን በቤተ መንግስት የችግኝ ተክለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ከዚህ በመቀጠል ለችግኞች እንክብካቤ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ጥሪ አቀረበዋል::

በአላዛር ታደለ

You might also like
Comments
Loading...