Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ዳኞች የስራ አፈጻጸም ምዘና ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ነሃሴ 19፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ዳኞች የስራ አፈጻጸም ምዘና ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዩኤስ ኤድ ፍትህ አክቲቪቲስ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ወጥና ከዳኝነት መርሆዎች የተጣጣመ መመሪያ ማዘጋጀታቸው ነው የተነገረው፡፡

መመሪያው የዳኝነት ስርዓቱን ውጤታማነትና ዳኞች ለሙያቸው ያላቸውን ተገዥነት በማሳደግ ለተገልጋዩ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እና ብቃትን በማሳደግ ተገቢ ያልሆነ አሰራርን ለማስቀረት እንሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም ዳኞች በሙያውና በስራቸው ላይ ያላቸውን ተነሳሽትና እርካታ ለማሳደግ፣ የአመራር አቅም በማሳደግ፤ የተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋት የፍርድ ቤቶችንን የህዝብ አመኔታ ለማሳደግ የዳኞች የስራ አፈጻጸም መመሪያ አስፈላጊ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የረቂቅ መመሪያው ይዘት ዳኞች የህግ እውቀታቸው፤ ቅንነት፣ታማኝነትና ገለልተኝነት፣ የተግባቦት ክህሎት እና ለሙያ ተገዢነት ናቸው፡፡

You might also like
Comments
Loading...