Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴር በሃምሌ ወር ከ17ቢሊየን 950ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል

አዲስ አበባ፣ነሃሴ 7፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በሃምሌ ወር ከ17 ቢሊየን 950 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ ።

ሚኒስቴሩ በዘንድሮ ዓመት የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረኮችን በመከወን የንግዱ ማህበረሰብ ግብር የመክፈል ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ  የህግ ማስከበር ስራዎችን መከናወኑን አስታውቋል።

በዚህም በሀገሪቱ የኋልዮሽ ይጓዝ የነበረውን የገቢ አሰባሰብ በጥሩ ሁኔታ  እንዲጓዝ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።

በዘንድሮዉ በጀት ዓመት ከ2010 በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር 22 ቢሊየን ብር ብልጫ ያለዉ ገቢ መሰብሰብ የታቻለ ሲሆን፥ከባለፈዉ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም ዘንድሮ በየወራቱ የሚሰበሰበዉ ገቢ እያደገ መጥቷል፡፡

በሃምሌ ወር 17 ቢሊየን 558 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 17 ቢሊየን 950 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉ ነው የተገለፀው።

ካለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀርም ከ26 በመቶ በላይ ብልጫ ያለዉ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ታማኝ ግብር ከፋዮችንና የተሻለ አፈፃፀም ያላቸዉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ዳይሬክቶሬቶች እዉቅናና ሽልማት በመስጠት የተሻለ ስራ በመስራት አገሪቱ ከምታመነጨው ኢኮኖሚ የሚገኘዉን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ የሚደርገዉን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ሰራተኛዉና አመራሩ እጅና ጓንት በመሆን በየወሩ የተሻለ ስራ በመስራት እንዲሁም በታማኝነት ግብራቸዉን በአግባቡ ለከፈሉ ግብር ከፋዮች ላበረከቱት አስተዋፅኦ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

 

 

You might also like
Comments
Loading...