Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ ስነ ስርዓት ተካሄደ፡፡

የምክር ቤቱ ምስረታ ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ነው የተካሄደው፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ አባገዳዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ አርቲስቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካለት ተገኝተዋል፡፡

ጨፌ ኦሮሚያ በ4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤው የዜግነት አገልግሎት አዋጁን በማጽደቅ የክልሉ መንግስት ስራ ላይ ያዋለው መሆኑ ይታወቃል፡፡

የምክር ቤቱን አረደጃጀት እና ተግባር በተመለከተ የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በዘንድሮው ክረምት በኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ለአረጋውያን እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ከ3 ሺህ በላይ ቤቶች ሲገነቡ፥ ከ4 ሺህ በላይ ቤቶች ደግሞ ጥገና እንደተደረገላቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በወሊድ ወቅት የደም መፍሰስ ለሚያጋጥማቸው እናቶች 4 ሺህ 556 ዩኒት ደም ተሰብስቧል ነው የተባለው፡፡

በአገልግሎቱም 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች የተሳተፉበት እንደሆነም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

You might also like
Comments
Loading...