Fana: At a Speed of Life!

የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በምሥራቅ የኢትዮጵያ ክፍል መስተዋሉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በምሥራቅ የኢትዮጵያ ክፍል መስተዋሉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እንቁላሉን በመጣል እና ዕጩን በማስፋፋት የሚታወቀው የአንበጣ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ መስተዋሉን በግብርና ሚኒስቴር የጸረ ተባይ መከላከል ዳይሬክተር አቶ ወልደ ሀዋርያት አስፋ ተናግረዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰተው የአንበጣ ወረርሽኝ ለመከላከል ከፌዴራል እና ከክልል የግብርና ቢሮ ጋር በቅንጅት እየተስራ መሆኑን ገልጸዋል።

የአየሩን ሁኔታ ተከትሎ አንበጣ ወረርሽን ሊኖር ስለሚችል አርሶ አደሮች መረጃዎችን ከግብርና ባለሙያ በመቀበል ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like
Comments
Loading...