Fana: At a Speed of Life!

የቱኒዚያው እጩ የፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ በታክስ ስወራ ክስ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ56 ዓመቱ የቱኒዚያ ዕጩ የፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ ናቢል ካሮይ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ከታክስ ስወራ ጋር በተያያዘ ክስ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ከዚህም ሌላ በካሮይ መስራችነት አገልግሎት ላይ የነበረው ነስማ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፈቃድ ሳይሰጠው የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ በማስተላላፉ እገዳ ተጥሎበታል ተብሏል፡፡

የፕሪዚዳንት ቤጂ ኢሰብሲ ህይወት ማለፍ ተከትሎ በአውሮፓዊያኑ ህዳር ወር በሃገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ምርጫው ወደ መስከርም15 ቀን 2019 ተዛውሯል ነው የተባለው፡፡

በዚህ ምርጫ ናቢል ካሮይን ጨምሮ 26 እጩ ተወዳዳሪዎች የቀረቡ ሲሆን÷ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር የሱፍ ቻሄድ አሸናፊ ይሆናሉ ተብሎ ግምት ተሰጥቷቸል ተብሏል፡፡

ተወዳዳሪዎቹ አሸናፊነታቸውን ለማዎጅ ከሃምሳ በመቶ በላይ ድምጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡

አንድም ተወዳዳሪ ይህን ድምጽ ማግኘት ካልቻለ ከአውሮፓዊያኑ ህዳር 3 ቀን 2019 በፊት ዳግም ምርጫ እንደሚጠበቅ ነው ዘገባው የሚስረዳው ፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን አፍሪካ

You might also like
Comments
Loading...