Fana: At a Speed of Life!

የሻደይ፣አሸንድዬና ሶለል በዓል በሚሊኒየም አዳራሽ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ነሃሴ 19፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የሻደይ፣አሸንድዬና ሶለል በዓል አዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ተከበረ፡፡
 
በበዓሉ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ፣ የባህልናቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳ ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ሌሎች የክልል እና የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
በርካቶች በታዳሙበት በዚህ በዓል በዓሉን የተመለከቱ የተለያዩ ስራዎች ቀርበዋል::
 
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ባደረጉት ንግግር ስብስባችሁ ለባህላችሁ፣ ለቅርሳችሁ እና ለእሴቶቻችሁ ያላችሁን ትርጉም የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንቷ ዛሬ ቅርሶቻችን የእኛ ብቻ ሳይሆኑ የዓለም ሕዝብ ቅርሶች በመሆናቸው የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓላትን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅመዋል፡፡
 
አሁን የምናጌጥባቸው እና የምንደምቅባቸው ቅርሶች የአያት ቅድመ አያቶች አሻራዎች እና የጥበብ ያሉት ፕሬዚዳንቷ ይህንን ያማረ ቅርስ ጠብቆና ተንከባክቦ ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ የትውልዱ ድርሻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓላት የመቻቻል፣ የደስታ፣ የፍቅር እና የአብሮነት መገለጫዎች ናቸው ብለዋል፡፡
 
እንደነዚህ አይነት በዓላትን በመጠበቅ ታላቅነታችን ማሳየት ይኖርብናል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡
You might also like
Comments
Loading...