Fana: At a Speed of Life!

የህጻናት የጀርባ ቦርሳ ክብደት በጤና ላይ እክል ስለሚያስከትል ጥንቃቄ ያስፈልጋል- ተመራማሪዎች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 22፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ደብረቶች፣ መጽሃፍቶች፣ የምሳ እቃ እና ሌሎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ብዛት የህፃናት ተማሪዎች የጀርባ ቦርሳ ክብደት እንዲጨምር ከሚያደርጉት ናቸው።

አዲሱ የትምህርት ዘመን ለመጀመር ከመቃረቡ ጋር ተያይዞ የአሜሪካ ኦርቶፔዲክ ባለሙያዎች ለወላጆች ለጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ ያጋሩትን መክር እንደሚከተለው አቅርበናል።

ምክንያቱም ከልክ ያለፈ ክብደት ያላቸው በጀርባ የሚታዘሉ ቦርሳዎች በህጻናት ልጆች ላይ የጀርባ፣ የአንገት እና ከትክሻ ጋር ተያያዠነት ያላቸውን ህመሞች ሊያስከትል ስለሚችል ነው ብለዋል።

ዶክተር አፍሺን ራዚ እንደተናገሩት፥ ከልክ ያለፈ ክብደት ያላቸውና በጀርባ የሚታዘሉ ቦርሳዎችን በማዘውተር የሚከሰት የጀርባ ህመም በበርካቶች ላይ ይስተዋላል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የጀርባ ህመም ወይም ጉዳቶችን ለመቀነስ ህጻናት ልጆች በጀርባ በሚታዘል ቦርሳዎች ውስጥ የሚይዙትን ነገሮች እንዲቀንሱ ማበረታታት አንዱ ነው ብለዋል።

ጤናማ ወይም ትክክለኛ የሰውነት ከብደት ያላቸው ህጻናት ከአጠቃላይ የሰውነት ክብደታቸው ከ10 በመቶ አሊያም 20 በመቶ ያልበለጠ ክብደት ያለው ቦርሳን እንዲሸከሙ እንደሚመከርም አስታውቀዋል።

ሆኖም ግን በርከት ያሉ ህጻናት በጣም ክብደት ያለው ቦርሳ ሲሸከሙ ይስተዋላል ያሉት ሲሆን፥ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ በቀን ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን ብቻ ነው መያዝ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ቦርሳቸውን ለመሸከም አሊያም ለማውረድ ከብዷቸው ሲታገሉ ከተመለከታችሁ የተወሰኑ መጽሃፍቶችን ከቦርሳው በመቀነስ በእጃቸው እንዲይዙ ማድረግ ማልካም ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ትምህርት ቤቶች የመጽሃፍቶችን ክብደት መቀነስ እንዲችሉ ማማከር እና ከተቻለ ደግሞ ሁሉንም መጽሃፍት ከሚሸከሙ ትምህርት ቤት የሚያሳድሩበትን ስፍራ ማመቻቸት ቢችሉም መልካም ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ www.upi.com

You might also like
Comments
Loading...