Fana: At a Speed of Life!

ዘመናዊ የወርቅና ብረት መጠቆሚያ መሳሪያ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 29 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዘመናዊ የወርቅና ብረት መጠቆሚያ መሳሪያን የሚገጣጥም ፋብሪካ ቢሮ በዛሬው እለት ተከፍቷል።

አልሂላሊ ጎልድ ማይኒንግ የተሰኘው ኩባንያ የወርቅ መጠቆሚያውን በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ ወርቅ አምራቾች ብሎም ለምስራቅ አፍሪካ የሚያቀርብ ነው ተብሏል።

በአዲስ አበባ ጎፋ አደባባይ አካባቢ የተገነባው ቢሮ ዘመናዊ የወርቅ መጠቆሚያ መሳሪያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።

ከማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው አልሂላሊ ጎልድ ማይኒንግ ኩባንያ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ባለሃብቶች ነው የተገነባው።

ፋብሪካው ስራውን በይፋ ሲጀምር የማዕድን ፍለጋ ስራዎችን የሚያቀሉ ቴክኖሎጂዎችን እንደሚያቀርብ ገልጿል።

በፋሲካው ታደሰ

You might also like
Comments
Loading...