Fana: At a Speed of Life!

አዲስ ወግ የውይይት መድረክ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ ወግ የውይይት መድረክ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ተካሄደ።

የውይይት መድረኩ “አንድ ጉዳይ የምጣኔ ሃብት ሪፎርም መነሻና አቅጣጫ” በሚል ርዕስ ነው የተካሄደው።

የፋይናንስ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ብሩክ ታዬ ባለፉት 17 ወራት የተተገበሩ አንኳር የማሻሻያ ስራዎችን ዘርዝረዋል።

በዚህም ዘላቂ መፍትሄ የሚሹ የዋጋ ግሽበት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የብድር አከፋፈልን የተመለከቱ ፖሊሲዎች፣ በንግድ ውስጥ ላሉና ወደንግድ ለሚመጡ ማነቆዎችን መፍታትና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር እንቅስቃሴዎች መደረጋቸውን ጠቅሰዋል።

በእነዚሁ ከአበዳሪዎች ጋር በመደራደር እፎይታ ለማግኘት የሚያስችሉ ማሸጋሸጊያዎችን ማድረግ፣ ያላለቁ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ማስጨረስና ሕጎችን የማብላላትና የመከለስ ስራዎች መሰራታቸውንም አንስተዋል።

አቶ መሳይ ታደሰ በበኩላቸው የፋይናንስ አቅርቦት ላይ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችንና ተግዳሮቶችን ባነሱበት ንግግራቸው፥ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሃገር ባለሃብቶች በሚኖር የብድር አቅርቦት፣ ከ28 በመቶ በላይ ሴቶችን የሚያሳትፉ ሶሻል ኢንተርፕራይዞች የሚመዘገቡበትና የሚተዳደሩበት አግባብና የብድር አቅርቦት እጥረት ዙሪያ መሰራት እንዳለበት አውስተዋል።

የንግድ እንደራሴ የሆኑት አቶ ብሩክ ፍቅሩ እንደገለፁት በወጭ ንግድ ላይ አለም አቀፍ አሰራርን የመረዳት ክፍተት ችግሮች ባጋጠሙ ወቅት ሙሉ በሙሉ መርምሮ የመረዳት አቅም ማዳበር አልተቻለም:።

የሕግና የአሰራር ማዕቀፎችም ባለሃብቶችንና የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ሳይሆን ግለሰቦችንም መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ መስራትና የተሻለ እቅድ የማስተባበር አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አዲስ ወግ የውይይት መድረክ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ መካሄዱ ይታወሳል።

ከአዲስ አበባ ውጭ ሲዘጋጅ የመጀመሪያ የሆነውና ሁለተኛው አዲስ ወግ የውይይት መድረክም በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል።

You might also like
Comments
Loading...