Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በበይነ መረብ 46 ሚሊየን ዶላር ያጭበረበሩ 80 ግለሰቦች ላይ ክስ መሰረተች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣ 2011(ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በበይነ መረብ 46 ሚሊየን ዶላር ያጭበረበሩ 80 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቷን አስታውቃለች።

የአሜሪካ ባለስልጣናት በይነ መረብን በመጠቀም በሚሊየን የሚቆጠሩ በርካታ ዶላሮችን ያጭበረበሩ 80 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረታቸውን አስታውቀዋል።

በወንጀሉ ከተጠረጠሩ ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ የናይጄሪያ ዜጎች መሆናቸው በዘገባው ተመልክቷል።

ከእነዚህ ወንጀለኞች ውስጥ 17 የሚሆኑት በቁጥጥር ስር ውለው ሎሳንጀለስ በሚገኘው ማረሚያ ቤት መታሰራቸው ተነግሯል።

ምርመራው የተጀመረው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2016 ላይ ሲሆን፥ በዚህም በርካታ ሰዎች በይነመረብን በመጠቀም የተለያዩ ሰዎችን ገንዘብ መመዝበራቸው ተረጋግጧል።

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን ለመፈጸምም ከተለያዩ ሰዎች ጋር  የውሸት የፍቅር ግንኙነቶችን በመመስረት በኦንላይን ገንዘብ እንዲሊኩ ያደርጉ ነበር ነው የተባለው ።

ከዚህ ባለፈም  የተለያዩ ትላልቅና ትናንሽ ቢዝነሶችን በጋራ እንሰራለን በማለት በውሸት አሳምነው ገንዘቡን በኦን ላይን እንዲሊኩ ያደርጉ የነበረ መሆኑ ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ እነዚህንና መሰል ዘዴችን በመጠቅም ከ46 ሚሊየን ዶላር ባላይ ገንዘብ ማጭበርበራቸው ነው የተገለጸው።

ይህም በአሜሪካ ታሪክ በበይነ መረብ አማካይነት የተፈጸመ ከፍተኛው የማጭበርበር ወንጀል መሆኑ ተጠቁሟል።

ምንጭ ፦አልጀዚራ

 

You might also like
Comments
Loading...