Fana: At a Speed of Life!

ነሃሴ 28 እና 29 በአዲስ አበባ ከተማ ሀገር አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የባህልናቱሪዝም ሚኒስቴር ነሃሴ 28 እና 29 ቀን 2011ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ ከተማ ሀገር አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፈረንስ እንደሚካሂድ አስታወቀ፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ የሆቴል ሙያ ማህበራት ኃላፊዎች እና የአስጎበኚ ድርጅቶች ማህበራት ተወካዮች በጉዳዩ ዙሪያ በዛሬው ዕላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ኮንፈረንሱ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተከሰቱ አለመረጋጋቶች የተነሳ የተቀዛቀዘውን ቱሪዝም እንቅስቀሴ ማነቃቃትን ታሳቢ ያደረገ ዓላማ እንዳለው በመግለጫው ተነስቷል፡፡

ባለፉት ጊዚያት አንዳንድ ከተሞች ተፈጥሮ የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ቀድሞ ወደነበረበት ሰላም መመለሱ ተገልጿል፡፡

በዘርፉ ላይ ጥሎት ያለፈውን ተፅኖ ከግምት በማስገባ ሰላም መመለሱን ለጎብኝዎችና ለመላው ዜጎች ግንዛቤ ማጨበጥ እስፈላጊ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ኮንፈረንሱ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ባለሃቶችና ሰራተኞች ተስፋ ቆርጠው ከቱሪዝም ዘርፍ ውጭ ያሉ አማራጮችን ሳያዩ በፍጥነት ወደ ስራ ለመመለስ የሚየስችል ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የቱሪዝም እንቅስቃሴው የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞች ማረጋገጥ እንደሚያስችል በዘገባው ተካቷለች፡፡

ኮንፍረንሱ አህጉራዊ ይዘት እንደሚኖረው ለማድረግ በቋሚነት እንደሚካሄድም ከባህልናቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like
Comments
Loading...