Fana: At a Speed of Life!

በ2011 በጀት ዓመት 791 የሚደርሱ የበይነ መረብ ጥቃቶችን መከላከል ተችሏል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት ሊያደርሱ የነበሩ 791 የሚደርሱ የበይነ መረብ ጥቃቶችን መከላከል ተችሏል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በ2011 በጀት ዓመት በተለያዩ ቁልፍ የሀገሪቱ ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች ላይ ሊፈጸሙ የነበሩ 791 የሚደርሱ የበይነ መረብ ጥቃቶችን ማክሸፍ መቻሉን አስታውቋል።

በኤጀንሲው የኢትዮጵያ ሳይበር የድንገተኛ ዝግጁነት እና ምላሽ ሰጭ ዲቪዥን ሃላፊ አቶ አብርሃም ገብረጻዲቅ፥ በሀገሪቱ ላይ ሊቃጡ የሚችሉ የበይነ መረብ ጥቃቶችን አስቀድሞ በመከላከል እና ከተከሰቱ በኋላ የከፋ ጉዳት እንዳያደርሱ አፋጣኝ  ምላሽ በመስጠት ረገድ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

ሃላፊው ጨምረው እንደገለጹት በ2011 በጀት ዓመት በሀገሪቱ ላይ የተቃጡ የበይነ መረብ ጥቃቶችን አስቀድሞ መከላከል በመቻሉ ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም በገንዘብ ሊተመን የማይችል ሰላም እና ፍትህን ማስጠበቅ መቻሉን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በቀጣይ 2012 በጀት ዓመት ሀገራዊ የበይነ መረብ ጥቃት የመከላከል ሽፋንን በማሳደግ እና ዓለም አቀፍ ትስስርንና ቅንጅትን በማጠናከር የሀገሪቱን ቁልፍ የበይነ መረብ መሰረት ልማቶች ደህንነት የማስጠበቅ ስራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

 

You might also like
Comments
Loading...