Fana: At a Speed of Life!

በ2011 በጀት ዓመት ከዱር ሙጫና ዕጣን ሽያጭ 96 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ትርፍ ተገኝቷል

 አዲስ አበባ፣ነሃሴ 6፣ 2011(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የግብርና ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከዱር ሙጫና ዕጣን ሽያጭ 96 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

ኮርፖሬሽኑ የሚሰጠውን የሜካናይዜሽን እና የኢንጂነሪንግ አገልግሎት ስራ ጨምሮ ለውጭ ሀገር ካቀረባቸው የዱር ሙጫና ዕጣን ሽያጭ 96 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ማትረፉን የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለፋናብሮድካሰቲግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በበጀት ዓመቱ ወደ ውጭ ከላካቸው የዱር ሙጫና እጣን ሽያጭ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ አግኝቷል።

አገልግሎት ከሰጠባቸው የሜካናይዜሽን እና የኢንጂነሪንግ አገልግሎት ስራን ጨምሮ ባአጠቃላይ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል።

ከዚህ ገቢ ውስጥ ከታከስ በፊት 96 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ማትረፍ መቻሉን የገለጹት ዳይሬክተሩ፥ በዚህም የእቅዱን 86 ከመቶ ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት ።

ኮርፖሬሽኑ የግብርና ምርት ማሳደጊያ፣ ምጥር ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የተለያዩ የግብርና ማሽነሪዎችና መለዋወጫዎችን ከማቅረብ ባሻገር የደን ውጤት ምርቶችን ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ መሆኑ  ይታወቃል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like
Comments
Loading...