Fana: At a Speed of Life!

በጃፓን በከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ 23 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 8 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን ከከፍተኛ ሙቀት ጋር በተያያዘ እስካሁን 23 ሰዎች መሞታቸውን የሃገሪቱ የእሳትና አደጋ መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ከ10 ቀናት በፊት ጀምሮ በሃገሪቱ ከፍተኛ ሙቀት መከሰቱ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም 12 ሺህ 751 ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት ተወስደው ክትትል እንደተደረገላቸው ኤጀንሲው አስታውቋል።

ለህክምና ወደ ጤና ተቋማት ካመሩት መካከልም 23ቱ መሞታቸውን ገልጿል።

ከሞቱት በተጨማሪም 400 ያክሉ ባጋጠማቸው ከፍተኛ የጤና እክል ሳቢያ የህክምና ክትትል ላይ ናቸው ተብሏል።

ክሮሳ ከተባለው አውሎ ነፋስ የሚነፍሰው ሞቃት አየር ለተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት መሆኑ ይነገራል።

 

ምንጭ፦ ሺንዋ

You might also like
Comments
Loading...