Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ1 ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ የኢቦላ ቫይረስ ተጋላጮች ክትባት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ ለኢቦላ ቫይረስ ተጋላጮች ለሆኑ ከ1 ሺህ 300 በላይ  ሰዎች ክትባት መስጠቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ባሳላፍነው ሳምንት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ አንድ በቫይረሱ አማካኝነት ህይወቱ ያለፈ ሰው ልጅ በቫይረሱ እንደተያዘች ይፋ ከተደረገ በኋላ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ሩዋንዳ ድንበሯን መዝጋቷ ይታወሳል።

ይህ ሰው ህይዎቱ ከማለፉ በፊት ከበርካታ ሰዎች ጋር ግኝኙነት እንደነበረው የተገለፀ ሲሆን፣ ቫይረሱ በፍጥነት ይዘመታል በሚል ስጋት ህዝብ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተደርጓል።

ለቫይረሱ ከፍተኛ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉት ዜጎች እና የዘርፉ ሙያተኞች የኢቦላ ቫይረስ መከላከያ ክትባት እንዲወስዱ መደረጉም ነው የተነገረው።

በዚህም ባሳላፍነው ሳምት ከላይ የተጠቀሰችው ህፃን በቫይረሱ ስለመበከሏ ሪፖርት ከተደረገ በኋላ አዲስ ታማሚ እንዳልተመዘገበ ነው የተገለጸው።

በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብክ ኮንጎ ጎማ ከተማ 2 ሚሊየን ያህል ዜጎች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል።

የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ለሚደረገው ጥረት በተለያዩ የሃገሪቱ ክልፍሎች የሚስተዋለው ጥቃት ተግዳሮት እንደሆነም መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በሀገሪቱ እንደገና በተቀሰቀሰው እና ለአንድ ዓመት ያህል በዘለቀው በኢቦላ ስርጭት በትንሹ 1 ሺህ 800 ያህል ሰዎች ሕይወት ማለፉ አይዘነጋም።

ምንጭ፡- ሲ.ጂ.ቲ.ኤን

You might also like
Comments
Loading...